ስትራቴጂያዊ የትኩረት መስኮች
1. የላቀ የህክምና አገልግሎት አሰጣጥ
ደረጃውን የጠበቀ የፈውስ፣ የማገገሚያና ህመም ማስታገስ፣ የድንገተኛና ጽኑ ህሙማን፣ የእናቶችና ህጻናት ህክምና አገልግሎት መሰጠትን ያካትታል፡፡ ይህም ሁሉን አቀፍ፣ ፍትሃዊ፣ ተደራሽ፣ ጥራቱ የተጠበቀ፣ ወጪ የሚቀንስ፣ ዘላቂነት ያለው፣ የህብረተሰብ ጤና ፍላጎት ላይ ያማከለ አገልግሎት በተቀናጀ መልኩ መስጠትና እንዲሁም የጾታ፣ የዕድሜ፣ የአካባቢ፣ የዘር፣ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልዩነት ሳይፈጠር ጥሩ የጤና አገልግሎቶችን ማቅረብን ያካትታል፡፡
- ስትራቴጂክ ውጤት፡-
- ለሁሉም ተደራሽ የሆነ ጥራቱን የጠበቀ የህክምና አገልግሎት ይኖራል፡፡ በህክምና አገልግሎት አሰጣጡ የሚያረካ አገልግሎት፡፡
2. የላቀ የጤና ማጎልበትና በሽታ መከላከል አገልግሎት አሰጣጥ ፡-
የመሰረታዊ የቤተሰብ የጤና አሀድ የጤና አገልግሎቶችን፣ የከተማ ጤና አከስቴንሽ ፓኬጆችን በመተግበርና ህበረተሰቡን በማሳተፍ ውጤታማ የበሽታ መከላከልና ጤና ማጎልበት ልምድ በኀብረተሰብ ደረጃ እንዲኖር ጥሩ የጤና ልማዶችን (የግል ንጽህና መጠበቅ፣ ሥርዓተ ምግብ፣ የአካባቢ ጤና) ማስፋፋት፤ ይህም የእናቶች፣ የህጻናት፣ የወጣቶች የአፍላ ዕድሜ ወጣቶች (Adolescents) በአጠቃላይ የህብረተሰቡን ጤና ተላላፊና ተላላፊ ካልሆኑ በሽታዎች መጠበቅን ያካትታል፡፡
- ስትራቴጂክ ውጤት፡-
- ጤናውን ማጎልበትና መጠበቅ የሚችል ህዝብ፣ በቁጥጥር ስር የዋለ የበሽታዎች ሥርጭት፡፡
3. የላቀ የህብረተሰብ ጤና አገልግሎት ፡-
የህብረተሰቡን የጤና ችግሮች በመዳሰስና በመለየት አፋጣኝ ምላሽ ለሚሹ ተግባራት ቅድሚያ በመስጠት በስራ ላይ ያሉትን የተለያዩ የምርምር ተቋማትና ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት በመተግበር ላይ ያለውን የጤና ፖሊሲና የአሰራር መመሪያ መነሻ በማድረግ የሕክምና አገልግሎት አሰጣጥ፤ የህክምና መገልገያ ግብዓቶች አቅርቦት፤ የጤናው ዘርፍ የቴክኖሎጂ የአጠቃቀም ሁኔታ፤ የክህሎት ማሰልጠኛ ማኑዋሎችና የጤና መረጃ ማመንጨት፤ መያዝና መጠቀምን እንዲሁም በቴክኒክና የጤና አስተዳደራዊ የአሰራር ክፍተትን በመለየትና በማህበረሰብ ጤና ምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ስልት በመታገዝ የጤና አመራር አካሉ የውሳኔ ሰጪነት ተግባሩን እንዲወጣ ድጋፍ መስጠት ይሆናል፡፡
- ስትራቴጂክ ውጤት፡-
- የህብረተሰቡን የጤና አገልግሎት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ያስችል ዘንድ የዘርፉን የአገልግሎት አሰጣጥ ሂደት በመዳሰስ ችግር ፈቺ የሆኑ ጥናትና ምርምር በማድረግ በመረጃ ላይ የተመሰረተ የውሳኔ አሰጣጥ አሰራር፡፡